top of page

በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ ፱፥፫

​ሳምንታዊ ጉባዔ ዘወትር ረቡዕ 6PM

​እንኳን ደህና መጡ

​እንኳን ወደ ደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ካቴድራል

ድረ-ገጽ በሰላም መጡ። ድረ-ገጹን ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኙ ከሆነ ወይም ዳግም ለመጎብኘት ተመልሰው ከሆነ አሁናዊ የካቴድራሉን መልዕክቶች ይመልከቱ።   

በቅርብ ቀን

የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ/ም 
የደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል ላስ ቬጋስ ቤ/ክርስቲያን 10ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል 

Feb 1 & 2, 2025 
Monthly Sermon & Liturgy in English

እንኳን ደህና መጡ

SS3

ስለ ቤተ ክርስቲያኑ

ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 13 ቀን 2015 እኤአ በኔቫዳ ግዛት ላስ ቬጋስ ከተማ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመ ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተክርስቲያኑ የመጀመሪያውን መንፈሳዊ አገልግሎት የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ/ም በኪራይ ቦታ የጀመረ ሲሆን በእግዚአበሔር ቸርነት ጽኑዕ የቤተ ክርስቲያኑ መስራች አባላት፣ ካህናት እና የልግስና አስተዋፅዖ አበርካቾች ለቤተ ክርስቲያኑ አሁናዊ እድገት ከፍተኛ የበረከት ሥራ ሰርተዋል።

SS1

ሰንበት ትምህርት ቤት

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመዋቅር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ክፍል አላት።

ሰንበት ትምህርት ቤቱ ፈለገ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ይባላል። ሰንበት ትምህርት ቤት በልጆቻችን መንፈሳዊ እና ግላዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ሰንበት ት/ት ቤቱ ታዳጊ ህጻናት እና ወጣቶች ስለዕምነታቸው የሚማሩበት፣ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚያውቁበት ፣ ጠንካራ የሞራል ስብዕና የሚያዳብሩበት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የማህበረሰብ እና የባለቤትነት ስሜትን የሚያዳብሩበት የመሠረት መድረክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

SS2

አግልግሎት

በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ፣ ቀኖናዊ ፣ ዶግማዊ ፣ ትውፊታዊ ሥርዓተ ትምህርት እና አጠቃላይ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣል።

ሳምንታዊ አገልግሎት


ረቡዕ | ጸሎት፣ ተከታታይ ትምህርት / ስብከት፣ መዝሙር።

ሐሙስ | የጠዋት ጸሎት፣ ቅዳሴ፣ ስብከተ ወንጌል እና መዝሙር።

ቅዳሜ | ትምህርተ ሃይማኖት እና የመዝሙር ልምምድ ለልጆች እና ወጣቶች።

እሁድ | የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ፣ ቅዳሴ፣ የሰንበት ት/ት ቤት ህጻናት እና ወጣቶች መዝሙር ፣ ስብከተ ወንጌል።

ሰኞ - እሁድ | የግል ጸሎት እና የምክር አገልግሎት።

 

ስብከተ ወንጌል እንዲናስፋፋ እና አገልግሎቱ እንዲጠነክር ቤ/ክርስቲያኑን ይርዱ

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፱፥፯

bottom of page