top of page
ሰንበት ትምህርት ቤት
የካቴድራሉ ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሕጻናትና ወጣቶችን ቆየት ያሉ እና በቅርብ የወጡ የመዝሙር ድርሰቶችን እንዲሁም ያሬዳዊ መዝሙሮችን በማሰልጠን የአምልኮ እና የምሥጋና መዝሙር በማቅረብ የሚያገለግል ጠንካራ የቤተ ክርስቲያኑ አካል ነው። በሰንበት ትምህርት ቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን መሠረት ያደረጉ የሃይማኖት ትምህርቶች ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ ተጨባጭ የህይወት ትምህርቶች የሚሰጥበት እና መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ ክህሎት ማሳያ መድረኮች የሚዘጋጁበት ጠንካራ ክፍል ነው። አገልግሎቱ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጥ ሲሆን ይህም ታዳጊዎች እና ወጣቶች የማህበረሰቡ አባልነታቸውን እንዲያሳድጉ እና ማንነታቸውን እንዲያጠናክሩ በመንፈሳዊ ህይወታቸው ጠንካራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ ያግዛል።

photo_2024-10-25_06-54-46_edited
Describe your image

SS
Describe your image

SS2_edited
Describe your image

photo_2024-10-25_06-54-46_edited
Describe your image
1/4
bottom of page
