top of page

የአብነት ትምህርት

የአብነት ትምህርት ሃይማኖታዊ የአገልግሎት ትምህርቶች የሚሰጡበት እና ተማሪዎች በግብረገብ እሴቶች የሚያድጉበት የቤተ ክርስቲያን ቀደምት የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። የአብነት ትምህርት ተማሪዎች የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሐዋርያዊ አስተምህሮዎችን እንዲያውቁ፣ በመንፈሳዊ ህይወት እንዲያድጉ እና የቤተ ክርስቲያን የወደፊት ተረካቢ አገልጋዮች እና መሪዎች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

​ስለ አብነት መምህሩ

የካቴድራሉ የአብነት መምህር የኔታ ቆሞስ አባ ግሩም አየለ ይባላሉ። በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ድጓ እና ቅኔ ትምህርቶችን ጠንቅቀው የጨረሱ እና ለረዥም ዓመታት በዚሁ ሙያ ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉ የአብነት መምህር ናቸው። በተጨማሪም የኔታ ግሩም ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ በሐዲሳት ትርጓሜ የዲፕሎማ ትምህርት መርሐግብር ያጠናቀቁ ናቸው።  

ይዘት

በካቴድራሉ የአብነት ስርዐተ ትምህርት ውስጥ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን የሚያካትት ሲሆን ትምህርቱን ለማጠናከር የእርስዎ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን እንገልጻለን። 

#የአማርኛ ፊደል ትምህርት #የግእዝ ቋንቋ ትምህርት #የግዕዝ ቁጥር ትምህርት  #የግብረገብ ትምህርት #ግብረ ዲቁና ትምህርት #የዜማ ትምህርት #የቅኔ ትምህርት #የትርጓሜ ትምህርት። 

 

በካቴድራሉ የአብነት መምህር የኔታ አባ ግሩም የሚሰጠው የአብነት ትምህርት ዘወትር ረቡዕ 6 pm – 8pm እና ቅዳሜ ከ3pm – 6pm ነው። በተጨማሪም ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በቀጠሮ ተማሪዎች ትምህርቱን ከመምህሩ መማር ይችላሉ።  

በተጠቀሰው የአብነት ትምህርት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ልጆቻችሁን ወደ ቤተ/ክርስቲያን በማምጣት እንዲማሩ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

bottom of page