top of page

ይለግሱ

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” 2ኛ ቆሮ 9:7

አባልነት

የአውቶማቲክ ክፍያ ዘዴ ማድረግዎን አይርሱ።

የአባልነት ወይም የልግስና ሁነቶችን ለማቀላጠፍ ሰበካ ጉባኤው በኦንላይን መስመር ፣ በቴክስት ጽሁፍ እና በካሽ የክፍያ አማራጭ ዘዴዎችን አዘጋጅቷል።

አባል ከሆኑ ወይም አባል መሆን እና የአባልነት ክፍያ መፈጸም ከፈለጉ፣ከዚህ በታች ያለውን የአባልነት ክፍያ የሚለውን ሳጥን ይጫኑ።

የገንዘብ ስጦታ

ጊዜዎን እና ችሎታዎን በፈቃደኝነት ለቤተ እግዚአብሔር በመስጠት ፣ ካቴድራሉ በሚያዘጋጀው የማህበረሰብ ተደራሽነት ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ፣ በካቴድራሉ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ወቅት አገልግሎት በመስጠት፣ ወይም ለቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በመለገስ የቤተ ክርስቲያን የልጅነት ድርሻዎን መወጣት ይችላሉ። ማንኛውም አስተዋጾ ትልቅም ይሁን ትንሽ በካቴድራሉ ትርጉም ያለው ሥራ ይሰራል። ስለሆነም ካቴድራሉን በተለያየ አርዕስት በገንዘብ ለመደገፍ ከዚህ በታች ያለውን ስጦታ የሚለውን ሳጥን ይጫኑ።

​ለውስጥ ጉልላት ማስከፈቻ ፕሮጀክት ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያን ጉልላት ውስጣዊ ክፍል ቅዱሳት ሥዕላት ተስለው ነገረ ምጽዐቱን እና ሰማያዊውን ሥርዓት የምናስብበት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን የስነ ሕንጻ ውበት መሆኑ ይታወቃል። የላስ ቬጋስ ደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል ካቴድራል ጉልላት ከፍታ ለቤተ ክርስቲያኑ እና ለአካባቢው ውበት ሲሆን በአንጸባራቂው ቀለሙ እና ጎልቶ በሚታየው የክርስቶስ መስቀል አርማ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ እና እያሳበ ያለ ውብ የስነ ሕንጻው ክፍል ነው። እንደ ሀገሩ የስነ ሕንጻ ህግ የውስጥ ጉልላቱ በድንገተኛ የእሳት አደጋ ጊዜ አውቶማቲክ ውሃ እንዲረጭ የሚያስችል ሲስተም ሊኖረው ይገባል። ሲስተሙ ሕንጻው ሲገነባ የተዘረጋ ቢሆንም በአካባቢው ካለው አነስተኛ የውሃ ግፊት አንጻር በካውንቲው የእሳት አደጋ እና መከላከል ኮሚሽን የሚጠየቀው የውሃ መጠን በማዕከላዊው የውስጥ ጉልላት ጫፍ ሊደርስ ባለመቻሉ  በካቴድራሉ አገልግሎት ከመጀመሩ አስቀድሞ የውስጥ ጉልላቱን ለመዝጋት ተገደናል። አሁን ላይ የካቴድራሉን ማዕከላዊ የውስጥ ጉልላት ለማስከፈት ፕሮጀክት ቀርጸናል። በዚህም የውሃ ግፊት መስፈርቶችን ለማሟላት  እና ጉልላቱን ለማስከፈት የሚያስፈልጉ የሥራ ቅድመ ዝግጅቶች አሉ። ለምሳሌ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል (3Phase power) ማስገባት ፣  አነስተኛ የውሃ ግፊቱን የሚጨምር ሲስተም (RPDA system) መቀየር  ፣ የውሃ ማቀባበያ እና መርጫ ሲስተም (Water pump system) ማስገባት። ይኽን ለማድረግ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚጠይቅ ሲኾን አሁናዊ አጠቃላይ ግምቱ $400,000 ነው።
የዚህን ፕሮጀክት ዓላማ ከግብ ለማድረስ የበኩልዎን አስተዋጽዖ ያድርጉ።  

Frequency

One time

Amount

$500

$1,000

$1,500

$2,000

Other

0/100

Comment (optional)

bottom of page