top of page
የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት
"ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫፥፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ወደ ክርስትና ሕይወት መግባትን የሚያመለክት ጥልቅ እና ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ሥርዓተ ምሥጢር ነው። ከጥምቀት ስርዓት በኋላ የዘለዓለም ህይወት የሚያሰጠው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ምሥጢር ለተጠማቂው ይፈጸማል ፣ በዚህም ተጠማቂው ወደ ቅድስና እና ከእግዚአ ብሔር ጋር ዘላለማዊ ኅብረት ያለውን መንገድ ይጀምራል። ልጅዎ እንዲጠመቅ ከፈለጉ ወይም እርስዎም ያልተጠመቁ እና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሥም አምነው መጠመቅ ከፈለጉ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ። ለጥያቄዎ ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን።
የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ
bottom of page