ሰበካ ጉባዔ
የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ ድህረ ገጽን ስለጎበኙ እናመሰግናለን። በካቴድራሉ እምነት፣ ፍቅር እና ኅብረት በአላማ የቆሙበት እንዲሁም ንቁ እና እንግዳ ተቀባይ ማህበረሰብ ያለበት ነው። የሰበካው አባላት ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቆ ለማስጠበቅ በተሰጠን አገልግሎት የጊዜ አስራት በማውጣት ለአገልግሎት ቆመናል። ለአካባቢው አዲስ ከሆኑ ወይም በከተማው የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አጥቢያ የሚሳተፉበትን መንገዶች እየፈለጉ ከሆነ እንኳን ደህና መጡ! ባለን አቅም በመንፈሳዊ አገልግሎት ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን።
በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ አባላት ለሦስት ዓመታት ያገለግላሉ። ከምዕመናን 3 አዲስ የሰበካ ተመራጮች በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በቤተክርስቲያኑ ጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣሉ። ከካህናት 2 አዲስ የሰበካ ተመራጮች በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በቤተክርስቲያኑ ካህናት ጉባኤ ይመረጣሉ። ከሰንበት ትምህርት ቤት 1 አዲስ የሰበካ ተመራጭ በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በቤተክርስቲያኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ይመረጣል። በእምነት ለማደግ እና ለማገልገል ፣ የቤተ ክርስቲያኑን ተልእኮ ለማስፈጸም በአባልነት ይቀላቀሉ።
የሰበካ ጉባዔ አባላት

Melake Bisrat Abba Admasie
Parish Admin

Mrs. Meskerem Arga
Treasurer

Liqe Diyakon
Yared Dagnew
Parish Secretary

Mr. Haile
Parish Sunday School Rep

Megabe Sirat
Kesis Assefa Desta
Parish Clergy Rep

Mr. Eyob Demsie
Accounts Manager

Mr. Hailemaryam Wolde
Parish Director
