top of page

ስለ እኛ

ራዕይ

የእግዚአብሔርን ክብር ፣ ፍቅር ፣ ቸርነት እና የማዳን ሥራ በመግለጥ ትውልዱ ሐይማኖቱን ጠንቅቆ እንዲያውቅ ማድረግ እና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። 

ተልዕኮ

በኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና እምነት የጠነከረ ማህበረሰብ በመገንባት ወንጌለ መንግስቱን ማስፋፋት፣

ደቀ መዛሙርት ማፍራት እና በአጥቢያችን የማህበረሰቡ የተስፋ እና የፍቅር ብርሃን መሆን ነው።

የእኛ ማህበረሰብ

ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ ማህበረሰባችን ከቤተክርስቲያኑ፣ ከባህላዊ ወጎቹ ፣ ቋንቋዎች እና ልማዶች ጋር ባለው ጥልቅ ትስስር ይታወቃል። ቤተክርስቲያናችንም በደማቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ስነ ስርዓቶች ፣ የስርዓተ አምልኮ ዝማሬዎች እና በፆም ወቅቶች ትታወቃለች። ኦርቶዶክሳዊ ማህበረሰባችንም እነዚህን ልዩ ገጽታዎች በማያወላውል አክብሮት ጠንቅቆ ይፈጽማቸዋል።

ታሪክ

ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላስ ቬጋስ በብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጪነት February 13 ቀን 2015 እኤአ በኔቫዳ ግዛት ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመ ለትርፍ ያልተቋቋመ ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተክርስቲያኑ የመጀመሪያውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ February 26, 2015 በኪራይ ቦታ የጀመረ ነው። የቤተ ክርስቲያኑ መስራች አባላት፣ የደብሩ መስራች ካህናት እና የልግስና አስተዋፅዖ አበርካች ኦርቶዶክሳውያ ለቤተ ክርስቲያኑ እድገት ወሳኝ ሚና አበርክተዋል። በእግዚአብሔር ቸርነት የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ አድራሻ 8245 Lindell Rd, Las Vegas, NV 89139 የሚገኘውን ባዶ ቦታ እና ይመኖሪያ ቤት ንብረት እኤአ ዲሴምበር 8 ቀን 2017 ዓ/ም መግዛት ችሏል። አዲሱን ካቴድራል ለመገንባት የደብሩ ሰበካ ጉባዔ እና ሕንጻ ኮሚቴ ከአጠቃላይ የደብሩ ምዕመናን እና ካህናት ጋር ባስቀመጠው ውሣኔ መሠረት እኢአ ሐምሌ 25 ቀን 2011 ዓ/ም የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቤተ ክርስቲያኑ መስራች አባት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ፣ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ እና አላስካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ በማድረግ ለአዲሱ ካቴድራል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ። ከሦሥት ዓመታት የግንባታ ጊዜ በኋላ አዲሱ የደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠናቆ በብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሐምሌ ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ወይም July 26, 2023 ተባረከ። ካቴድራሉን የባረኩ ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል የኦሃዮ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብጹዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ እና አላስካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብጹዕ አቡነ ናትናኤል የኮሎራዶ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ አማሮ ቡርጂ ጌዴኦ እና ምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እና የደብሩ መስራች ሊቀ ጳጳስ ናቸው።

ጥቂት ስለ ቤተ ክርስቲያኑ እድገት 

  • የቤ/ክርስቲያኑ ሕጋዊ ምሥረታ Feb 13, 2015 እኤአ

  • የመጀመሪያው ቅዳሴ ቤት Feb 26, 2015 እኤአ

  • ለቤ/ክርስቲያኑ የሕንጻ ግንባታ የቦታ ግዢ Dec 18, 2017 እኤአ

  • የመሠረት ድንጋይ ለቤ/ክርስቲያኑ የሕንጻ ግንባታ July 25, 2019 እኤአ

  • የሕንጻ ቤ/ክርስቲያኑ ግንባታ ውል Dec 22, 2019 እኤአ

  • የካቴድራሉ ምርቃት (ቅዳሴ ቤት) July 26, 2023 እኤአ

እምነትዎን አግኝተዋል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለዎትን እምነት ጠንቅቀው እንዲጠብቁ እና እንዲያሳድጉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

መንፈሳዊ እርካታን እየፈለጉ፣ የማህበረሰብ ስሜት እንዲኖርዎ ፣ ወይም እግዚአብሔርን በማምለክ ጉዞዎ ላይ ያለዎትን እምነት የበለጠ ለመረዳት እንዲችሉ ለማድረግ የቤተ ክርስቲኗ በር ክፍት ነው።

bottom of page