top of page

ንስሐ ግቡ!
ስብከተ ወንጌል
"ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።" ማር 16፡15
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጥንታዊ እና በቤተ ክርስቲያኗ ተልእኮና ማንነት ውስጥ ጉልህ ሚና ያለው ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ካሉ አንጋፋ ጥንታውያን የክርስትና ማኅበረሰቦች አንዷ ናት። የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል በመዋቅር አደረጃጀቱ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ክፍል ያለው ሲሆን በአሁን ሰዓት ክፍሉን የሚመሩት መጋቤ ሐዲስ መምህር ድጋፌ ገብረሚካኤል ናቸው።
የስብከተ ወንጌል መርሐግብር
ረቡዕ
ረቡዕ በየሳምንቱ 6Ppm-8pm
ሐሙስ
ሐሙስ በየሳምንቱ ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ
ወርኃዊ ጉባዔ
በዕለተ ቅ/ገብርኤል 6Ppm-8pm
እሑድ
እሑድ በየሳምንቱ ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ
ይከታተሉ
በካቴድራሉ በቀጥታ ስርጭት ከሚተላለፍ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ወይም የተቀረጹ የስብከት ቪዲዮዎችን በዚህ ገጻችን ላይ በማኖር ለሰው ልጅ ሁሉ ጠቃሚ የሆነውን የመንግስቱን ወንጌል ለማስፋፋት ጥረት እናደርጋለን። ግባችን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶቻችን እና መንፈሳዊ መልዕክቶች ለእርስዎ በሚመች ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ ነው። በተመቸዎት አጋጣሚ በዚህ ገጽ ላይ ከእኛ ጋር እንዲገናኙ እናበረታታዎታለን፣ በዚህ ገጽ ላይ የቅርብ ጊዜ የስብከት ቪዲዮዎችን ለእይታ ዝግጁ ሆነው ያገኛሉ። በቅርቡ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ የጽሁፍ መልዕክቶችንም እዚሁ ያገኛሉ። ድረ-ገጻችንን ስለጎበኙ እናመሰግናለን።
bottom of page


